የአገዛዙ የክስ ድርሰት…

በመጨረሻም አገዛዙ ከ6 ወር እስራቸው በኋላ የክስ ድርሰቱን ፅፎ ጨርሷል።
ዮሐንስ ቧያለው፣ #ክርስቲያን ታደለ፣ #እስክንድር ነጋና #ዘመነ ካሴና ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱን ጨምሮ በ52 ግለሰቦች ላይ የሽብር ወንጀል ክስ ተመሰረተ

ዮሐንስ ቧያለውና ክርስቲያን ታደለ እና ጋዜጠኛ እና የሰብዐዊ መብት ተሟጋቹ አባይ ዘውዱን  ጨምሮ በ52 ግለሰቦች ላይ የሽብር ወንጀል ክስ ተመሰረተ፤ ክሱን የመሰረተው የፍትህ ሚኒስቴር የተደራጁና ድንበር ተሻጋሪ ጉዳዮች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት ጀነራል ነው።

በተከፈተው ክስ ዝርዝር ላይ እንደተገለጸው፤ ተከሳሾች የፖለቲካ ርዕዮትን በኃይል ለማስፈፀም በማሰብ የሚለው ይገኝበታል ያለው ዘገባው ተከሳሾች ያደራጁትን የአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤትን ዓላማ ለማስፈፀም ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ተሰብስበዉ በመደራጀት፤ የአማራ ሕዝብ “ሀገር ተወስዶበታል ርስቱን ተቀምቷል” የሚል አቋም በመያዝ የአማራ ርስት ናቸው የሚሏቸዉን መሬቶች በወታደራዊ ኃይል ለማስመለስና ሀገርን ‹‹በአማራ እሳቤ ብቻ መገዛት አለባት›› በሚል ስምምነት ላይ ደርሰዋል የሚል እንደሚገኝበት አስታውቋል።

ከ90 በላይ የመንግስት እና የግለሰቦች መኪኖች እንዲዘረፉ እና እንዲወድሙ እንዲሁም ለአርሶ አደር የሚከፋፈሉ ከ9 ሺህ ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ የዘረፉ እና እንዲዘረፉ ያደረጉ በመሆኑ የሚል ክስም እንደተመሰረተባቸው አመላክቷል።
https://t.me/Moamediamoresh

© 2024 AGPA