በድሮን ጥቃት በርካታ ንፁሃን ተጨፈጨፉ!
በሸዋ ይፋት ቀጠና በቀወት ወረዳ የለን ቀበሌ ጉሎ ትምህርት ቤት ላይ ዛሬ ግንቦት 4/2016 ዓ.ም ሁለት ጊዜ በተከታታይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በርካታ ንፁሃን ተገድለዋል።
ከተገደሉት ውስጥ የትምህርት ቤቱ ሰራተኞች የሆኑ 4 መምህራን ይገኙበታል።
ከ27 በላይ ንፁሃን ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። እግራቸውን እና እጃቸውን በድሮን ጥቃት ያጡት ወገኖች ህክምና ተቋም መድረስ ባለመቻላቸው ብዙ ደም ፈሷቸው ሕይወታቸው እያለፈ ነው ሲሉ ምንጮች ገልፀዋል።
ባለፉት 11 ወራት በዐማራ “ክልል” ከ90 ጊዜ በላይ የድሮን ጥቃት ተፈጽሞ 512 በላይ ንፁሃን መጨፍጨፋቸውን ምንጮች አስተውሰዋል።
በድሮን ጥቃት በርካታ ንፁሃን ተጨፈጨፉ!