ግፍ እና አስነዋሪ ድርጊት እየተፈጸመብን ነው!

እጅግ በጣም አስነዋሪ ድርጊትና ግፍ እየተፈፀመብን ነው‼️

የሕዝብ ተመራጮች የኾኑት ክርስትያን ታደለ፣ ዮሃንስ ቧያለው፣ ካሳ ተሻገርና ጋዜጠኛ እና የለብዐዊ መብት ተሟጋች እና ጋዜጠኛ አባይ ዘውዱን ጨምሮ በሜክሲኮ ፌደራል የምርመራ እስር ቤት የሚገኙ 11 ተጠርጣሪዎች “አካላዊ፣ ሞራላዊና ሥነ ልቦናዊ ጥቃት” እየተፈጸመባቸው እንደኾነ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለጠቅላይ ፍርድ ቤትና ለፍትህ ሚንስቴር በደብዳቤ አቤቱታ ማቅረባቸውን ዶይቸቨለ ዘግቧል። ተጠርጣሪዎቹ በደብዳቤያቸው፣ ለከፍተኛ የምግብ እጥረትና ለጊዜያዊና ቋሚ በሽታዎች ተጋላጭ እንድንኾንና ከቤተሰብ፣ ከጠበቃ፣ ከኃይማኖት አባቶች፣ ከመብት ድርጅቶችና ከሌሎች ጠያቂዎች ጋር እንዳንገናኝ ተደርገናል ማለታቸውን ዘገባው አመልክቷል። ዘገባው፣ ተጠርጣሪዎቹ የአምሓራ ማንነታቸው እየተጠቀሰ ማዋረድ፣ ስድቦች፣ ዘለፋዎች፣ ዛቻዎችና አካላዊ ጥቃቶች (ድብደባዎች) እንደተፈጸሙባቸው ጠቅሰዋል ብሏል። ፌዴራል ፖሊስ ጉዳዩ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መርማሪ ቦርድን እንደሚመለከት በመግለጽ፣ በአቤቱታው ዙሪያ ምላሽ እንዳልሰጠ ዜና ምንጩ ጠቅሷል።
https://t.me/Moamediamoresh

© 2024 AGPA