በ #ኦሮሚያ ክልል በሁለት ዞኖች በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት በርካታ የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮችን እና ምዕመናንን መግደላቸው ተነገረ
በኦሮሚያ ክልል #ምዕራብ_አርሲ እና #ምሥራቅ_አርሲ ዞኖች ታጣቂዎች በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቀሳውስት እና ምዕመናን ላይ በፈጸሟቸው ጥቃቶች በርካታ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ።
በምዕራብ አርሲ ሀገረ ስብከት በዶዶላ የደብረ ቅዱሳን ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሁለት አገልጋዮች ከነሙሉ ቤተሰቦቻቸው ሰኞ መጋቢት 16/2016 ዓ.ም. ባልታወቁ ታጣቂዎች መገደላቸውን ተገልጿል።
ከዚህ ግድያ አንድ ቀን ቀደም ብሎ መጋቢት 15/2016 ዓ.ም. አንድ የ80 ዓመት ሴት አዛውንት እና ሌላ ወጣት ምሥራቅ አርሲ ውስጥ በአስቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።
በምሥራቅ አርሲ ዞን የቤተክርስቲያኗ አገልጋይ እንደተናገሩት ቤተክርስቲያንን እና ምዕመናንን ዒላማ ባደረጉ ጥቃቶች ከመስከረም 2016 ዓ.ም. ወዲህ በአካባቢው ከ80 ያላሱ ሰዎች ተገድለዋል።
https://t.me/Moamediamoresh